በኢትዮጵያ ከክርስቶስ መወለድ ሁለት ሺህ ዘመናት አስቀድሞ የቋንቋ ማስረጃዎች ተገኝተዋል። በሀገሪቱ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የግዕዝ ቋንቋ በአራተኛው ክፍለዘመን ክርስትና የቤተመንግሥቱ ሃይማኖት ከሆነ ጀምሮ እጅግ ብዙ የሆኑ የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የፍልስፍና እና የተለያዩ ዘውግ ያላቸው መጽሐፍት፣ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች እንዲሁም ሌሎችም ተጽፈዋል።

በግዕዝ ከተጻፉ ጽሑፎች ሁሉ እስካሁን ትልቅ ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት ኤርትራ ውስጥ መተራ በሚባል ቦታ የተገኘው ሃውልት ላይ የተጻፈው ጽሑፍ ሲሆን በመቀጠል ትግራይ አቡነ ገሪማ ገዳም ውስጥ የሚገኘው ወንጌል ተመዝግበው ከተያዙ የግዕዝ የወረቀት ወይም የብራና ላይ ጽሑፎች ሁሉ የሱን ዕድሜ የሚወዳደር አልተገኘም

በመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ሁለት ዐበይት ነገሮችን ማንሳት ይቻላል አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እና ፍትሐ ነገሥት። በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን የነገሱት አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። እንዲሁም እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ እንደ ሕገመንግሥት ሲያገለግል የነበረው ፍትሐ ነገሥት ከአረብኛ ተተርጉሞ እና ተስተካክሎ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረውም በዚሁ ዘመን ነው።

በእስልምና አራተኛዋ ቅዱስ ከተማ ተብሎ የሚቀፀልላት ጥንታዊቷ ሀረር በሀገራችን የእስልምና የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ቀዳሚውን ድርሻ ትወስዳለች።

ከአስራ ስድስተኛው ክፍለዘመን ጀምሮ በጽሑፍ ላይ ጉልበቱ እያየለ የመጣው አማርኛ፣ ከአማርኛ ወደላቲን መዝገበ ቃላት ተዘጋጅቶለት ወደላቲን የተተረጎመ የመጀመሪያው የአፍሪቃ ቋንቋ ለመሆን በቃ።

ዘመናትን የተሻገረው ሥነ ጽሑፋችን በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ግን ያለው ድርሻ ከታሪክ እኩዮቻችን አንፃር በነበረት የቀጠለ እንዲያውም ከተሰቀለበት ማማ የወረደ ሆኗል። ታሪክን ከትቦ ማስቀመጥ፣ ሐሳብን በጽሑፍ መግለፅ፣ በተጻፈ ነገር ላይ ተመስርቶ ሐሳብ መሰንዘር፣ ዕውቀትን በንባብ ማዳበር እና የመሳሰሉት ገና ብዙ ልንጓዝበት የሚገባን መንገድ ነው።

ሎሚ የመጽሐፍት መደብር መተግበሪያ ከዘመኑ ነባራዊ ሁኔያ ጋር ሊጓዝ የሚችል፣ አንባቢያን መጽሐፍ መርጠው፣ መጽሐፍ ገዝተው፣ መጽሐፍ የሚያነቡበት ትልቅ መፍትሄ ነው። የደራሲያንን የሕትመት ላይ ውጥንቅጥ በመቀነስ፣ የአባብያንን የቴክኖሎጂ ምርጫ መሠረት በማድረግ፣ በማኪያቶ ዋጋ መጽሐፍትን አቅርቧል።

ሎሚ ለትውልድ ግንባታ የበኩሉን ጥረት ያደርጋል።

Want to work with us? Get In Touch